We’ve updated our Terms of Use to reflect our new entity name and address. You can review the changes here.
We’ve updated our Terms of Use. You can review the changes here.

ስ​ለ​እ​ኔ የ​ሚ​ማ​ል​ደ​ው ኢ​ዩ​ሱ​ስ ነው Selene Yemimaldew

by Zerfie Kebede

supported by
liyuwork
liyuwork thumbnail
liyuwork ሰለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ
እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት
እመሰክርለታለሁ÷ ማቴ 10÷32....በጌታሽ ፊት ዋጋ አለሽ እና በርቺ...በነገር ሁሉ ፀጋ ይብዛልሽ!!!
parisonic
parisonic thumbnail
parisonic Amen, Amen, Amen. Beautiful. Thank you and God bless.
Eshetu Meshesha Bahiru
Eshetu Meshesha Bahiru thumbnail
Eshetu Meshesha Bahiru እጅግ በጣም የምወድሽና የማከብርሽ ዘርፌ የአገልግሎት ዘመንሽ ይባረክ። በውስጥሽ ያለው ፀጋ የከበረ ነው። You are one of my best gospel singer.
/
1.
2.
WELETAH 08:00
3.
4.
MENFES QEDUS 04:45
5.
6.
7.
8.
9.
10.
11.
12.
DEMU NEW 05:14

about

ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።
(ዮሐ.15፡13)
በበደላችንና በኃጢአታችን ሙታን የነበርነውን የሰው ልጆች ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ ክብሩን ትቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ራሱን በቀራንዮ መስቀል የሰጠልን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘመናችንን ሁሉ ብንዘምርለት አይበቃም። እርሱ ሁሉን የፈጠረ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለና አንድ የሆነ የዘላለም አምላክ ሆኖ ሳለ ስለኛ ሰው ሆኖ በመስቀል ላይ በመሞት ከራሱ ጋር አስታረቀን። እንደዚሁም በርሱ የመስቀል ሥራ ልጅነትን ካገኘን በኋላ በዚህች ዓለም በሚገጥመን ውጣ ውረድ ሊረዳንና ሊያግዘን እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነት የዘላለም ሊቀ ካህናችን ሆኖ ወደ ቅድስት በመግባት በክብሩ ዙፋን ተቀመጠ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ታላቅና ዘላለማዊ ሊቀ ክህነቱ ሲያስተምረን «እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል። እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤ ይለናል።(እብ.7፡22-26) በአራተኛው ምዕራፍም ላይ።
«እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ። ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።» በማለት ክርስቲያኖች የሆንን ሁላችንም በየዕለቱ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንድንቀርብ ያበረታታናል። እኔም በዚህ አዲስ ዝማሬየ ይህንን ላደረገው አምላክ ክብርና ምስጋናየን አቀርባለሁ።

credits

released February 12, 2018

ኃጢአተኛ እያለሁ ምሕረቱን በኔ ላይ አብዝቶ በታላቅ ፍቅሩ ለወደደኝና በደሙ አጥቦ የራሱ ላደረገኝ ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችንም ለኢየሱስ ክርሰቶስ ክብርና ምስጋና ይሁንለት።

license

all rights reserved

tags

about

Zerfie Kebede Seattle, Washington

በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ። ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል። መዝ.104:33-34
እጅግ የምወዳችሁና የማከብራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በእግዚአብሔር ቸርነትና ምሕረት የቆምኩ እህታችሁ ስለ እናንተም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆንኩ እኔ ከሁሉ አስቀድሜ የረዳኝን ልዑል እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። እንዲሁም
በአገልግሎቴና በሕይወቴ ሁሉ ከጎኔ ለቆማችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦቼ ምስጋናየ ብዙ ነው።
«በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።» 2.ቆሮ.4:6
... more

contact / help

Contact Zerfie Kebede

Streaming and
Download help

Redeem code

Report this album or account

If you like Zerfie Kebede, you may also like: